Home / News / በሰሜን ጎንደር በመንቀሳቀስ የግድያና አፈና ተግባር ሲያከናውኑ በቆዩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በሰሜን ጎንደር በመንቀሳቀስ የግድያና አፈና ተግባር ሲያከናውኑ በቆዩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ሐምሌ 5፣2008

በሰሜን ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የተለያዩ የግድያና የአፈና ተግባር ሲያከናውኑ በቆዩ ተጠርጣሪ ወንጀሎኞች ላይ ረጅም ጊዜ የፈጀ ክትትል ሲደረግና ተጨባጭ ማስረጃ የማሰባሰብ ሥራ ሲሰራ ከቆየ በኋላ ከፍርድ ቤት ህጋዊ የመያዣ ፍቃድ በማውጣት የፌዴራል ፖሊስ ልዩ የፀረ ሽብር ቡድን በዛሬው ዕለት እርምጃ ወስዷል፡፡
ኤርትራና በሌሎች የውጭ አገራት ከሚገኙ አሸባሪና ፀረ ሰላም ሃይሎች የጦር መሳሪያ ገንዘብና መመሪያ እየተቀበሉ ሲንቀሳቀሱ የቆዩት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ወንጀለኞች ሲፈጽሟቸው ከቆዩት በርካታ ወንጀሎች መካከል ሰኔ 07/2008 አንድ ሰላማዊ ዜጋ በማፈንና በማገት ከቤተሰቦቹ በርከት ያለ ገንዘብ ለመዝረፍ ሙከራ አድርገዋል ሰኔ 21/2008 ዓ.ም በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዳንሻ ከተማ ጨለማን ተገን በማድረግ በጦር መሳሪያ አንድ ሰው ገድለዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በዚህ ወር በተለያየ ጊዜ በጠገዴ ወረዳ ጉርቢና ሰርቆ በተባሉ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ በመንግስትና በህዝብ ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርሱ ቆይተዋል

የግብረሀይሉ መግለጫ እንዳመለከተው  ተጠርጣሪ ወንጀለኞቹ ከኤርትራና ከሌላ የውጭ አገራት  በሚሰጣቸው የተለያየ ዓይነት ድጋፍ እየታገዙ ለተከታታይ የአፈናና የግድያ ተግባር እራሳቸውን በከፍተኛ ደረጃ በማደራጀት ላይ የነበሩ ናቸው፡፡

በዚህ መሠረት የብሔራዊ መረጃና የደህንነት አገልግሎት እና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ ለማቅርብ በወሰነው መሠረት አብዛኞቹ በዚሁ ተከታታይ የሆነ የአፈናና የግድያ ተግባር ላይ ተሰማርተው የቆዩት ተጠርጣሪዎች ወንጀለኞች ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ሲደረግ ሁለቱ ግን አሻፈረን በማለት በህግ አስከባሪዎች ላይ ተኩስ በመክፈት አደጋ አድርሰዋል፡፡

በህግ አስከባሪዎች ላይ ተኩስ ከከፈቱት ሁለቱ ተጠርጣሪ  ወንጀለኞች መካከል አንዱ በመኖሪያ ቤቱ የነበረውን ሰው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተኩሶ በመግደል መሽጎ ከነበረበት ቤት በማምለጥ ለጊዜው ተሰውሯል፡፡

ሁለተኛው ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ቤተሰቡንና ልጆቹን በጋሻነት አግቶ በመያዝ ተጠርጣሪ ወንጀለኛውን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተሰማራው የፌዴራል ፖሊስ ልዩ የፀረ ሽብር ቡድን በቤተሰቡና በልጆቹ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ባሳየው ገደብ የለሽ ትእግስት ምክንያት ተጠርጣሪው ወንጀለኛ አጋጣሚውን ተጠቅሞ በተኮሰው ጥይት አንድ የልዩ ፀረ ሽብር ቡድን አባል የተገደለ ሲሆን ይኸው ተጠርጣሪ ወንጀለኛ የተፈጠረውን ግርግር በመጠቀም ለተባባሪዎቹ ባስተላለፈው የድረሱልኝ መልእክት ተጠርጣሪ ተባባሪዎቹ ከየነበሩበት ተጠራርተው በመምጠት ፎቅ ላይ በመውጣት በከፈቱት ተኩስ በሁለት ተጨማሪ የልዩ ቡድኑ አባላት የሞት በሌሎች አምስት አባላት ላይ ደግሞ የማቁሰል ጉዳት አድርሰዋል፡፡

በፌዴራል ደረጃ የሚፈጸምን ወንጀል የመከላከልና የማክሸፍ ኃላፊት የተሰጠው የፌዴራል መንግስታዊ አካል በማንኛውም የአገሪቱ አካባቢ የህዝብን ህይወትና ንብረትና  የመከላከልና የመጠበቅ ስልጣን የተሰጠው ቢሆንም ለህግ አስከባሪ ሐይሎች እጃችንን አንሰጥም በማለት አሻፈረን ባሉ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ቤተሰብና ልጆች ላይ አደጋ እንደይደርስ ባሳዩት ከልክ ያለፈ ትእግስት ምክንያት ለኦፕሬሽኑ የተሰማሩ ሶስት የፌዴራል ፖሊስ ልዩ የፀረ ሽብር ቡድን አባላት ህይወታቸውን አሳልፈው ለመስጠት የተገደዱበት ሌሎች አምስት የህግ አስከባሪ አባላት ደግሞ የቆሰሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ችሏል፡፡

በዚህ ትእግስትና ጥንቃቄ የተሞላበት ህጋዊ እርምጃ ምክንያት በጀግንነትና በከፍተኛ የሙያ ዲስፕሊን ክቡር ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ልዩ የፀረ ሽብር ቡድን አባላት ታሪክ ለዘላለም ይዘክራቸዋል ያለው መግለጫው በዚህ አጋጣሚ እስካሁን ባለው መረጃ በተፈጠረው ግርግር በተባራሪ ጥይት የአንድ ሰው ህይወት ከማለፉ በቀር በሰላማዊ ሰው ህይወትም ሆነ ንብረት ላይ የደረሰ ሌላ ጉዳት እንደሌለ ገልጿል፡፡

ከኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶችና የእነሱ ተላላኪ በሆኑ አሸባሪዎችና ፀረ ሰላም ኃይሎች በሚሰጣቸው መመሪያና የተለያየ ዓይነት ድጋፍ የአገራችን ሰላምና አንድነት ለማናጋት የሚንቀሳቀሱ ወንጀለኞች መቼም ይሁን የትም ከህግ እንደማያመልጡ በዚህ አጋጣሚ በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን ሲል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረሃይል ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

About Amora

If your Content posted here, in our youtube, twitter and Facebook pages and you want us to modify or remove it, please email us using the contact form in our site. Thanks.

Check Also

Egypt warns Ethiopia Nile dam dispute is life or death -El-Sissi

El-Sissi sought to reassure Egyptians in televised comments while attending the inauguration a fish farm in the Nile Delta province of Kafr el-Sheikh, but stressed that “water is a matter of life or death.” “No one can touch Egypt’s share of water,” he said.

Qatar, Ethiopia sign pact on investment protection

Qatar and Ethiopia have finalised and signed an investment protection agreement on Tuesday, according to HE the Minister of Economy and Commerce Sheikh Ahmed bin Jassim bin Mohamed al-Thani.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *