ተመድ ሶስተኛውን ግዙፍ ፅህፈት ቤቱን በ56 ሚሊየን ዶላር በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዓለም በትልቅነቱ ሶስተኛ ደረጃን የሚይዝ ፅህፈት ቤቱን አዲስ አበባ በ56 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለመገንባት ፕሮጀክት ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገለፀ።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ በኒውዮርክ የተባበሩት መንግስታ ድርጅት የማዕከላዊ ድጋፍ አገልግሎት ረዳት ዋና ፀሃፊና የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሃፊ ስቴፈን ከትስ የተመራ ሰባት አባላት ያሉት የልዑካን ቡድንን በብሔራዊ ቤተመንግስት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ይህ የተገለፀው።

በዚሁ ወቅት ፕሬዚዳንቱ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽን አባል ሀገር እንደመሆኗ ቀደም ሲል የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መቀመጫ እንዲሆን ፅህፈት ቤት ሰርታ መስጠቷን ተናግረዋል፡፡

ይህንኑ ለማሻሻልና ታሪካዊ ቅርስነቱን በጠበቀ ሁኔታ ዘመናዊ ማስፋፊያ ለማከናወን ለሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ መንግስት ፈቃደኝነት ቀደም ሲል መገለፁን ጠቅሰዋል፡፡

See more at: FBC

About Amora

If your Content posted here, in our youtube, twitter and Facebook pages and you want us to modify or remove it, please email us using the contact form in our site. Thanks.

Check Also

Egypt warns Ethiopia Nile dam dispute is life or death -El-Sissi

El-Sissi sought to reassure Egyptians in televised comments while attending the inauguration a fish farm in the Nile Delta province of Kafr el-Sheikh, but stressed that “water is a matter of life or death.” “No one can touch Egypt’s share of water,” he said.

Qatar, Ethiopia sign pact on investment protection

Qatar and Ethiopia have finalised and signed an investment protection agreement on Tuesday, according to HE the Minister of Economy and Commerce Sheikh Ahmed bin Jassim bin Mohamed al-Thani.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *