ኤርትራ: ሰላም ፈላጊ ህዝብ የተፈጠረባት፣ ሰላም የሚፈልግ መንግስት ግን የሚያስፈልጋት

ከጥቂት ዓመታት በፊት በኤርትራ የነበረኝ አመለካከት አሁን ካለኝ ሃሳብ በፍጹም የተለየ ነበር:: ኤርትራ ከኢትዮጵያ ሰላም አርጋ ትኖራለች የሚል እምነት ለአንድ ደቂቃ አስቤም አላቅም:: ኤርትራ የኢትዮጵያ ቁጥር 1 ጠላት ናት የሚል ጽኑ እምነት ነበረኝ:: ያ አመለካከት ከስሜት የተነሳ አልነበረም::አሁን  ሃሳቤን የቀየርኩትም በምኞት ላይ የተመሰረተ አይደለም::

ሻብያ ስልጣና ከያዘባት ቀን ጀምሮ ህዝቡን ትምክህትና ጥላቻ በስፋት አስተምረዋል
 • የኤርትራ ህዝብ የተለየን ነን
 • እኛን የሚመስል ህዝብ የለም
 • ኢትዮጵያዉያን በተለይ ትግራዋይ ደመኛ ጠላትህ ናቸው
 • እኛ ነን ኢትዮጵያ ነጻ ያወጣናት
 • በፈለግነው ግዜ ወያነ ከስልጣን ማውረድ እንችላለን
 • እትዮጵያ የሚትባል አገር አትኖርም: ትበተናለች
 • ትምክህትና ጥላቻ ከማስተማር ጎን ለ ጎን ፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን ማስታጠቅና ማደራጀት፣ እንደ አልሸባብ ያሉ አክራሪዎች ከመደገፍም አልቦዘነም
 • በነገራችን ላይ የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ማስታጠቅ የጀመረው ከጦሩነቱ በፊት፣ በሰላም ግዜ ጀምሮ ነበር
የኤርትራ ህዝብ መልስ
 • ያሁሉ ትምክህትና ጥላቻ በብዙ ኤርትራኖች ተቀባይነት አገኘ
 • ትምክህትና ጥላቻ የሚሰብኩ ዘፈን፣ድራማ ና ኮመዲ ብስፋት ተሰርተዋል
 • ብዙ ቁጥር ያለው ኤርትራዊ ተታለለ
 • በኤርትራ ሲኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዉያን በተለይ ደግሞ የትግራይ ተወላጆች ንብረታቸው ተቀሙ፣ተገደሉ ፣የተለያዩ ግፍ ደረሰባቸው
 • በየእንተርኔቱ ኢትዮጵያን ማንቃሸሽ በስፋት ቀጠሉበት
የትምክህትና ጥላቻ ዉጤት
 • ዉጤቱ ግልጽ ነው
 • የኤርትራ ህዝብ እንደማንኛውም ህዝብ መሆኑን በጋህድ ታየ
 • የኤርትራ ህዝብ በማንኛውም ግዜ አይቶትና ሰምቶት የማያውቀው ችግር ገብተዋል
 • በየወሩ 5000 የሚደርሱ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ ይሰደዳሉ፣ያልተሳካላቸው ደግሞ ይገደላሉ ይታሰራሉ
 • የተሻለ ሂዎት ለማግኘት ወደ ሌላ አገር በሚያደርጉት አደገኛ ጉዞ መደፈር ፣መታሰር ፣መደብደብና ሞት ያጋጥማቸዋል
 • የዉስጥ አካለቸው ተሽጦ የተረገሙት አረቦች እድሜ ማራዘሚያ ሆኖዋል
ግዜው ቢረዝምም
 • አሁን ነገሮች ተቀይረዋል
 • ኢትዮጵያዉያን የኤርትራዉያን ወዳጆች እንጂ ሻብያ እንዳለው ጠላት አለመሆናችን በተግባር አስመስክረናል
 • የኢትዮጵያ ዳርድምበር ከተሻገሩባት ደቂቃ ጀምሮ ቦርደር አከባቢ ያለው ህዝብና ሰራዊት በሚያደርጉለት አቀባበል የአብዛኛዉን የተሳሳተ አመለካከት ቀይረዋል
 • ብዙ ኤርትራዉያን በድፍረት በPaltalk, Facebook ና በመሳሰሉት መንገዶች በድፍረት ኢትዮጵያ ወዳጅ አገር መሆንዋን እየመሰከሩ ይገኛሉ
 • በብዝዎቹ ኤርትራዉያን የነበራቸው የተሳሳተ ዕምነት ተቀይረዋል
 • ሰላም ፈላጊ ህዝብ ተፈጥረዋል ፣ ሰላም የሚፈልግ መንግስት ግን የሚያስፈልገዋል
ለወደፊት ምን መደረግ አለበት?
 • በሁለቱም አገሮች ሰላም እንዳይኖር ያደረገው ዋናው እንቅፋት ተወግደዋል
 • የሻብያ የትምክህትና የጥላቻ ፕሮፖጋናዳ  ሰሚ አጥተዋል
 • ሻብያ የህዝብ ድጋፍ አጥተዋል
 • ከኢሳያስና ጥቂት አመራሮች ዉጪ ሻብያ አለ ብሎ ለመናገርም አያስደፍርም
 • በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያ ከሚሰደዱት ዉስጥ የኤርትራ ወታደሮች ይገኙበታል
 • እነኝህ ወታደሮች ማደራጀትና ማስታጠቅ ያስፈልጋል
 • እነኝህ ወታደሮች ለአመታት በተለያዩ ቦታዎች በዉትድርና ሲያገለግሉ ስለቆዩ ፣ስለሻብያ ሰራዊት የተሟላ መረጃ አላቸው
 • የተቀረው የሻብያ ሰራዊትም የመዋጋት ፍላጎት የለዉም:: ፍላጎት ቢኖሮው በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያ ባልመጣ ነበር::
 • ኢሳያስ አፈወርቂ አርጅቶ እስኪሞት ድረስ አንጠብቅ::  ስርዓቱ መወገድ አለበት:: ኢትዮጵያ ልክ ከ ሱዳን፣ከጅቡቲ ና ከንያ ያላትን ጥሩ ግንኙነት ፣ ከኤርትራም ያስፈልጋታል:: ለዛም ኢትዮጵያም ግዴታዋን መወጣት አለባት::

About Amora

If your Content posted here, in our youtube, twitter and Facebook pages and you want us to modify or remove it, please email us using the contact form in our site. Thanks.

Check Also

Egypt warns Ethiopia Nile dam dispute is life or death -El-Sissi

El-Sissi sought to reassure Egyptians in televised comments while attending the inauguration a fish farm in the Nile Delta province of Kafr el-Sheikh, but stressed that “water is a matter of life or death.” “No one can touch Egypt’s share of water,” he said.

Qatar, Ethiopia sign pact on investment protection

Qatar and Ethiopia have finalised and signed an investment protection agreement on Tuesday, according to HE the Minister of Economy and Commerce Sheikh Ahmed bin Jassim bin Mohamed al-Thani.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *