አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከግንቦት ሰባት መሪዎች የሽብር ተልዕኮ በመቀበል በትግራይና በሰሜን ጎንደር ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በፀጥታ አካላት ላይ ተኩስ በመከፈት ጉዳት ያደረሱ አምስት ተከሳሾች በ10 አመት በጽኑ እስራት ተቀጡ።
የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ተከሳሾች 1ኛ አብርሃም ዘውዴ፣ 2ኛ ትዛዙ ወልደመድህን፣ 3ኛ ሽባባው አዲሱ፣ 4ኛ አደላድሌ ተስፋ እና 5ኛ ገዛኸኝ መሃሪ ናቸው።
የጠቅላይ አቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመላክተው ተከሳሾቹ ኤርትራ በመሄድ ራሱን የአርበኞች ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራው የሸብር ቡድን አመራሮች ከዶክተር ብርሃኑ ነጋ፣ ከማአዛው ጌጡና ከኮማንደር አሰፋ ማሩ በድብቅ ህዝቡን ለሽብር አላማ ለመቀስቀስ፣ በመንግስት ላይ ለማሳመፅ እንዲሁም ተኩስ በመክፈት ህዝቡን ማሸበር የሚሉ የሸብር ተልዕኮዎችን ተቀብለዋል።
READ MORE AT :FBC