Home / News / የተፈጠረውን ሁከት በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ ጥረቱን እንዲያጠናክር ግብረ ሃይሉ አሳሰበ

የተፈጠረውን ሁከት በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ ጥረቱን እንዲያጠናክር ግብረ ሃይሉ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረውን ሁከት በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር እያደረገ ያለው ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ጸረ ሽብር ግብረ ሃይል አሳሰበ፡

ግብረ ሃይሉ በወቅታዊው የክልሉ ጸጥታ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ካለፈው ህዳር ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በአንዳንድ የከፍተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ውስን ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች የሆኑ ተማሪዎች ከፊት ለፊት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም ከበስተጀርባ ከውጭ ዘወትር ለሀገራችን ህዝቦች ሠላምና ዕድገት እንቅፋት መሆናቸውን በገሃድ ካስመሰከሩ የሽብር ቡድኖች የሚሰጣቸውን ተልዕኮ አንግበው ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር ቀጥተኛ ትስስር በመፍጠር ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን አስተጓጉለዋል ነው ያለው ግብረ ሀይሉ፡፡

እንዲሁም ከትምህርት መዋቅሩ ውጭ የሚገኘውና ከፍ ሲል ከተገለጸው የሽብር ቡድን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ ግንኙነት በመፍጠር የነውጡና ረብሻው አድማስ ወደ ከተሞችና ወደተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲስፋፋ በማድረግ በርካታ የመንግስት፣ የግል ባለሃብቱና የደሃው አርሶ አደር ንብረትና ሃብት እንዲወድም አድርጓል ብሏል የግብረ ሀይሉ መግለጫ፡፡

የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት ለመጠበቅ በተሠማራው የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ አባላትና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሞትና የአካል መጉደል አደጋ መድረሱንም አመላክቷል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ግብረ ሃይል ህገ መንግስታዊ ስርዓትንና የህዝቡን ሰላማዊ የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት ለማረጋገጥ፤ አስተማማኝ ለማድረግ በሽብርና በአመፅ ሃይሉ ላይ የሚያደርገውን ህጋዊና ተመጣጣኝ እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል፡፡

የፀረ-ሽብር ግብረ ሃይሉ ይህንን እርምጃ በተከታታይነት ሲወስድ መላው የኢትዮጵያ ህዝበ እንደ ከዚህ ቀደሙ አካባቢውን በመጠበቅና ከፀጥታ ሃይሎች ጎን በመቆም የበኩሉን እንዲወጡ ያስገነዘበ ሲሆን፥ በተለይም ችግሩ ጎልቶ በሚታይባቸው አካበቢዎች የሚኖሩ ዜጎች እስካሁን የሽብርና የአመጽ ሀይሎችን እኩይ ተግባር ከማክሸፍና አካባቢያቸውን ከመጠበቅ ባሻገር ከጸጥታ ሀይሎች ጎን በመቆም እየተፋለሙ የህይወት መስዋዕትነት ጭምር እየከፈሉ እንደሚገኙም ጠቁሟል።

ለዚህም ግበረ ሀይሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሚገኙ የከፍተኛና ሁለተኛ ደረጃ የሚማሩ ተማሪዎች በርካቶቹ ሂደቱን በመቃወምና በመኮነን ትምህርታቸውን እየቀጠሉ የሚገኙ ከመሆኑም በላይ መደበኛ ትምህርቱን ወደጎን በመተው የሽብርና የአመፅ ሃይሉ ሰለባ የሆኑ ተማሪዎችን አጋልጦ በመስጠትና የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ለማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በገጠርም ሆነ በከተማ የሚኖረው ህዝብ አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት በትምህርት ተቋማትም ሆነ ከትምህርት ተቋማት ውጭ የሚገኙትን ልጆቹንና መላ ቤተሰቡን የሰው ህይወት እንዳይጠፋና ንብረት እንዳይወድም፣ ዘረፋ እንዳይስፋፋ፣ የሽብር የአመጽ አቀጣጣዩች ሰለባ እንዳይሆን በማድረግ የበኩሉን ሚና እንዲጫውትም ግብረ ሃይሉ መልዕክቱን አስተላልፏል።

Source: www.fanabc.com

About Amora

If your Content posted here, in our youtube, twitter and Facebook pages and you want us to modify or remove it, please email us using the contact form in our site. Thanks.

Check Also

Egypt warns Ethiopia Nile dam dispute is life or death -El-Sissi

El-Sissi sought to reassure Egyptians in televised comments while attending the inauguration a fish farm in the Nile Delta province of Kafr el-Sheikh, but stressed that “water is a matter of life or death.” “No one can touch Egypt’s share of water,” he said.

Qatar, Ethiopia sign pact on investment protection

Qatar and Ethiopia have finalised and signed an investment protection agreement on Tuesday, according to HE the Minister of Economy and Commerce Sheikh Ahmed bin Jassim bin Mohamed al-Thani.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *